ማንቼስተር ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 2 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
የዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ምቤሞ፣ ፈርናንዴዝ (በፍጽም ቅጣት ምት) እና ኩለን (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ በተካሄደው ጨዋታ የበርንሌይን ግቦች ደግሞ ፎስተርና አንቶኒ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በጨዋታው ማንቼስተር ዩናይትድ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ድል አስመዝግቧል፡፡