Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ በሲድኒ የማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲድኒ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ አሸንፏል።

በዓለም አትሌቲክስ ሜጀር ማራቶን ውስጥ በተካተተው 2025 የሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።

በዚህም በወንዶች አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቋል።

እንዲሁም አትሌት አዲሱ ጎበና 2 ሰአት ከ06 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በተመሳሳይ በሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ እና ሲጫላ ቁሜሺ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ፤ ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፋለች።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.