መርከቦቻችን አምባሳደር ሆነው ኢትዮጵያን እያስተዋወቁ ይገኛሉ – በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) መርከቦቻችን አምባሳደር ሆነው ኢትዮጵያን እያስተዋወቁ ይገኛሉ አሉ።
በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ተቋሙ በወጭ እና ገቢ ንግድ ላይ የየብስ እና የባህር ላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶች እቃዎችን በማጓጓዝ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
ኢባትሎ ከለውጡ ወዲህ መዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ አገልግሎቱን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን አንስተው፤ የኢትዮጵያ መርከቦች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ኢትዮጵያን እያስተዋወቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ተቋሙ ባለው አካዳሚ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሙያዎች በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን ማመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አክለውም እንደ ግብርና፣ ከተማ ልማት፣ ማኑፋክቸሪነግ እና መሰረተ ልማት ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ዓመታዊ ገቢ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ወጭ እና ገቢን ምርትን በማሳለጥ ጊዜ ቆጣቢ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ገንቢ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!