Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

የቦረና ዞን፣ የያቤሎ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህዝቡ የገዳን ሥርዓት ጠብቆ ያቆየ፣ የሀገሩን ድንበር ሲጠብቅ የኖረ ነው ብለዋል።

የቦረና ሕዝብ ኤልሶድ (ጨው ቤት) ከሚባለው ሥፍራ ጨው እያመረተ ኢትዮጵያውያንን ሲመግበን ኖሯል፤ ለዚህም እናመሰግናለን ነው ያሉት።

በድርቅ ሲፈተን የነበረው ቦረና ያ ሁሉ አልፎ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሚያስችል መንገድ ላይ ነን ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን ድርቅና ረሃብን የትናንት እንጂ የዛሬና ነገ ታሪካችን አካል አይሆኑም ብለዋል።

የቦረና ህዝብ ለዘመናት የዘለቀ የውሃ አጠባበቅና አቀማመጥ ባህል እንዳለው አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

መንግሥት በሁሉም አካባቢ ፈጣን ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ የሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርትን ማስፋፋትም ልማምተን ለማፋጠን ጉልህ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

የመንግስት ፖሊሲ ውጤት የሆነው የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ የቦረና ዞን ህዝብ የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄን የመለሰ፣ የአካባቢውን እምቅ የልማት ፀጋ ለመጠቀም ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የቦረናን ባህል፣ ታሪክ፣ የገዳ ሥርዓት፣ የያቤሎን የአዕዋፍ መናኸሪያ፣ የቦረናን ፓርክ ለማየትና ለማድነቅ ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁሉም አቅጣጫ የሚኖሩትን የሀገራችንን ህዝቦች በማገናኘት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና በመወጣት ላይ ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የበለጠ እንዲያስፋፋ እና እንዲያዘምን መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.