Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 217 ሺህ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የምስክር ወረቀት ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ 217 ሺህ 611 በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የምስክር ወረቀት ወስደዋል አለ የከተማ አስተዳደሩ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አዋሌ መሃመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ በመዲናዋ በቴክኖሎጂ የታገዘና ዘመኑን የዋጀ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በ5 ሚሊየን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ አሁን ላይ 423 ሺህ 517 ወጣቶች ሥልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

217 ሺህ 611 ወጣቶች ደግሞ ስልጠናውን በሚገባ ተከታትለው በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል ነው ያሉት ሃላፊው፡፡

የዲጂታል ኢኮኖሚን ማሳለጥ የሚያስችለውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወጣቶች እንዲወስዱ ኮሚቴ ተዋቅሮ የግንዛቤ መፍጠር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ቢሮዎችና በ11ዱ ክ/ከተሞች በተካሄደ የንቅናቄ ሥራ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡

በመዲናዋ ዲጂታል ኢኮኖሚን ማሳላጥ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.