Fana: At a Speed of Life!

ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ ሼህ መሀመድ ሸሪፍ ደግሞ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠዋል፡፡

በተጨማሪም ሼህ ሀቡድን ኑራ ደግሞ የስራ አመራር ፀሃፊ ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል።

ምክር ቤቱ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫንም ያከናወነ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በአምስት ዘርፎች የሚወክሉ የምክር ቤት አባላትን መርጧል።

የአዲስ አበበ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በጀማል አህመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.