በዛሬው ዕለት የተደረጉ ዝውውሮች…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን በርካታ ተጫዋቾች ወደተለያዩ ክለቦች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ፡፡
ሊቨርፑል የክለቡ ክበረወሰን በሆነ 130 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አሊክሳንደር ኢሳክን ከኒውካስል ዩናይትድ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ በአንፊልድ ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ይፈርማል፡፡
በሌላ ዝውውር ማንቼሰተር ሲቲ ጣሊያናዊውን ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ በ30 ሚሊየን ፓውንድ ከፒኤስጂ ለማስፈረም የተስማማ ሲሆን፥ ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት ምሽት ወደ እንግሊዝ በማቅናት ለሲቲ ፊርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ ብራዚላዊው የማንቼሰተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ሞሪያስ የቱርኩን ፌነርባቼ ተቀላቅሏል፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ አንቶኒ ሳንቶስ የስፔኑን ሪያል ቤቲስ በቋሚ ዝውውር ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡
በሚኪያስ አየለ