Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከባየር ሊቨርኩሰን ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግን አሰናብቷል፡፡

አሰልጣኙ ከማንቼስተር ዩናይትድ ከተሰናበቱ በኋላ ያለ ክለብ የቆዩ ሲሆን፥ በዚህ ክረምት ስፔናዊውን ዣቢ አሎንሶ ተክተው ባየር ሊቨርኩሰንን መረከባቸው ይታወሳል፡፡

ሊቨርኩሰን በቡንደስሊጋው ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ የተለያየ ሲሆን፥ ማግኘት ከነበረበት ስድስት ነጥብ ማሳካት የቻለው አንዱን ብቻ ነው፡፡

የክለቡ አመራሮች ባለፉት ሳምንታት የቡድኑን እንቅስቃሴ በመገምገም አሰልጣኙን ለማሰናበት ውሳኔ ማሳለፋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎ ምክትሎቻቸው በጊዜያዊነት የአሰልጣኝነት ኃላፊነቱን እንደሚረከቡ ክለቡ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.