Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ አዲስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ቤልጂየማዊውን ግብ ጠባቂ ሴን ላሜንስ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ዩናይትድ ለግብ ጠባቂው ዝውውር ለቤልጂየም ፕሮ ሊጉ ሮያል አንትወርፕ 21 ሚሊየን ዩሮ የሚከፍል ይሆናል፡፡
ተጫዋቹ ለአምስት ዓመታት በኦልድትራፎርድ የሚያቆየውን ውል እንደሚፈርም ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ ባለፉት ቀናት ከአርጄንቲናዊው ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.