ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን ማለፍ የምትችለው ኪነጥበብን መጠቀም ስችል ነው – ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን ማለፍ የምትችለው ኪነ ጥበብን መጠቀም ስችል ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2017 የሚቆይ ‘ጥበባት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚያካሄደው ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የኪነ ጥበብ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።
ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ የኪነ ጥበብ ውድድሩ የኢትዮጵያ ማንሰራራት እውን በሆነበት ሰዓት የምናካሂደው በመሆኑ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ማብሰር ነው።
ቀጣዩ 2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ልዩ ዓመት እንደሚሆን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያ ህልም ከሚታሰብ ህልም ወደ ሚጨበጥ የሚሸጋገርበት ዓመት በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
እንደ ኪነ ጥበብ ከወቀሳ ቀደ ሙገሳ የተሸጋገርንበት ነው በማለት ገልጸው፤ አሁን የኢትዮጵያን ጸጋዎች፣ ዕድሎች፣ ተስፋዎች፣ ቀጣይ ምዕራፎች እያነሳን ኢትዮጵያን የምናሞግስበት ጊዜ እንደሆነ አመልክተዋል።
ህብራዊነት ለኢትዮጵያ መልኳ ነው፤ ኪነ ጥበብ ይሄንን ማሳየት፣ ተስፋ መስጠት እና ማብሰር እንዳለበት በማንሳት ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን ማለፍ የምትችለው ኪነ ጥበብን መጠቀም ስትችል እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በማንሳት አደባባዮቻችን፣ መንገዶቻችን፣ የኢትዮጵያን ሕብር የሚያሳይ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
ይሄ የለውጥ ዘመን ደግሞ ለኪነ ጥበብ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል ነው ያሉት።
ከዚህ ውድድር ነገ ኢትዮጵያን የሚያስጠሩ ሰዎች እንደሚወጡ እና ሌሎች ተሰጥኦቸውን ራሳቸውን ለማሳየት እንዲነሳሱ ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፤ የኪነ ጥበብ ውድድሩ የሀገራችን የጥበብ ዘርፍ እምቅ አቅም አጉልቶ ለማሳየት፣ ተተኪ እና ወጣት ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ትልቅ መድረክ ነው።
የሀገራችን ጥበብ እንዲያድግ ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ ከማዘጋጀት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንም አመልክተዋል።
ጥበባት የሀገር ገጽታን የሚገነባ፣ ለባህል ልውውጥ እና ዲፕሎማሲ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ዘርፍ መሆኑን በተግባር በማረጋገጥ ‘ኪን ኢትዮጵያ’ የባሕል እና የኪነጥበብ ቡድን በማደራጀት የኢትዮጵያን ባህል ታሪክ ወግ እና ቋንቋ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲታይ መደረጉንም ጠቁመዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!