Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ

አዲስአበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል መንግስት አዲስ ዓመት እና የመውሊድ በዓልን በማስመልከት ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋርቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ከለውጡ ወዲህ እየተከናወኑ ባሉ ሰው ተኮር ስራዎች የኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆነው የመደጋገፍ ባህል እየጎለበተ መጥቷል።

ማዕድ ማጋራት የእርስ በርስ ትስስራችንንና አብሮነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም መተሳሰባችንን የምንገልፅበት የሰው ተኮር እሳቤያችን የተግባር ማሳያ ነው ብለዋል።

መሰል ተግባራት የኑሮ ጫናን በመቀነስ ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው÷ ሁሉም ህብረተሰብ የመደጋገፍ ባህልን ይበልጥ ሊያጎለብትና አቅመ ደካማ ወገኖችን ሊያግዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.