በሁሉም ዘርፎች የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተያዘው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል አሉ።
የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
አቶ አረጋ ከበደ በመድረኩ እንዳሉት፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶቹ የተሻለ ዝግጅት ተደርጎባቸዋል።
ዕቅዶቹን በመተግበር እና ለህዝብ የልማት ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የአመራሩ ቁርጠኝነት እና በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዚህም በክልሉ በሁሉም ዘርፎች እቅዶችን ማሳካትና የሚጠበቁ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚገባ ገልጸው፤ ለዚህም ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ ላይ በ2017 በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ባህር ዳር ከተማ፣ ደብረ ብርሃን ከተማና ኮምቦልቻ ከተማ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዞን ደረጃ ደግሞ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ወሎ በተመሳሳይ ሽልማትና እውቅና ማግኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።