የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኮን ሚቼል በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ተቀብለዋቸዋል።
ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ “ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ጉባዔው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በደቡብ ደቡብ የትብብር መንፈስ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት፣ አፍሪካ ከካረቢያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር ለማሳደግ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጉባዔው በዓለም የፋይናንስ ስርዓት፣ በቱሪዝም፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ይመክራል።
በአሸናፊ ሽብሩ