ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጽናታችን እውነተኛ ተምሳሌት ነው – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ኩራታችንና የጽናታችን እውነተኛ ተምሳሌት ነው አሉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ግድቡ ለምረቃ መብቃቱን በማስመልከት ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ መልዕክት ፥ የዘመናት ቁጭት በቆራጥ ሀገር ወዳድ መሪና ሕዝብ ወደ ድል ተሸጋግሯል ብለዋል።
የደም፣ የላብ እና የውሃ ጠብታ ዋጋ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለኢትዮጵያዊያን መበሰሩን አውስተዋል።
ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ኩራታችን፣ የኢኮኖሚ አቅማችን፣ የጽናታችን እውነተኛ ተምሳሌት እና የትብብራችን ውጤት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡