በመዲናዋ የሕዳሴ ግድብን የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶና ስዕል ዓውደ ርዕይ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “ኢትዮጵያ ትችላለች” በሚል መሪ ሃሳብ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና ስዕል ዓውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፍቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ነው የፎቶ እና የስዕል ዓውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለእይታ ክፍት ያደረገው፡፡
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እና በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተገኝተዋል።
እንዲሁም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራልና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡