Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኒኩሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም ቁርጠኛ ናት – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለሁሉን አቀፍ ዕድገት የኒኩሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም ቁርጠኛ ናት አሉ።

በኦስትርያ ቬና እየተካሄደ በሚገኘው 69ኛው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ላይ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፤ ኒኩሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም አብራርተዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ ሀገራዊ እድገት ያግዛት ዘንድ የኒኩሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አላማ ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዳሴ ግድብን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ይፋ ካደረጓቸዉ ፕሮጀክቶች መካከል የኒኩሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል መሆኑን ያስታወሱት በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ ኤጀንሲው ፕሮጀክቱን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የኒዉክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ማለትም ለሀይል አቅርቦት፣ ለምርምር፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለአካባቢ ጥበቃ መጠቀም ያስችላት ዘንድ በፈረንጆቹ ከ1957 ጀምሮ የየኤጀንሲው አባል መሆኗ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.