አቶ አረጋ ከበደ በጎንደር እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የአማራ ክልል አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
በጉብንታቸውም ከአፄ ቴዎድሮስ አየር መንገድ አዘዞ ኮሌጅ እስከ ፒያሳ ድረስ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡
ከፍተኛ አመራሮች በቆይታቸው ከመሰረ ልማት ስራዎች ጉብኝት ባሻገር በከተማዋ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን እንደሚመርቁ ይጠበቃል።
በምናለ አየነው