Fana: At a Speed of Life!

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ታሳቢ ያደረገ የትውልድ ግንባታ ላይ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል ኢትዮጵያ ዓላማዎችንና ዓለም የደረሰበትን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘመን ታሳቢ ያደረገ የትውልድ ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የክረምት ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ 300 ታዳጊዎችን ባስመረቀበት ወቅት ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በዚሁ ወቅት÷ ዘመኑን የሚዋጁና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አብዮት ጋር የሚናበቡ እንዲሁም የሚመጣውን ጫና መቋቋም እንድንችል ታዳጊዎች ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ይህ ትውልድ እኛ ያለፈን ዕድል ሊያልፈው አይገባም፤ ሊወርስ የሚገባውም ግጭት፣ ጦርነት እና ችግር መሆን የለበትም ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

ለታዳጊዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ትልቁን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መገንባቷን በማስታወስ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ እውን የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለያዩ መመዘኛዎች ለምረቃ የበቁ ታዳጊዎች በመደበኛ ትምህርቶቻቸው ላይ መበርታት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋ፡፡

በሌይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.