Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ – ተጠባቂው ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 12:30 አርሰናል ማንቼስተር ሲቲን በኢምሬትስ የሚያስተናግድበት መርሐ ግብር ተጠባቂ ነው።

በሁሉም ውድድሮች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በማንቼስተር ሲቲ አንድም ሽንፈት ያላስተናገዱት መድፈኞቹ ይህንን ሪከርድ ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል ሁለቱን እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲዎች አንድ ጊዜ ያሸነፉ ሲሆን፥ በሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል።

በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አርሰናል አትሌቲኮ ቢልባኦን እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ናፖሊን በተመሳሳይ 2 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

የምሽቱን ጨዋታ የ42 ዓመቱ ስቱዋርት አትዌል በመሐል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

በሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ቦርንማውዝ በቪታሊቲ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ኒውካስል ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ በሊጉ እስካሁን ግብ ማስቆጠር ያልቻለው አስቶን ቪላ ከሜዳው ውጭ ሰንደርላንድን ይገጥማል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.