Fana: At a Speed of Life!

ሰላምን በማጽናት የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ የጸጥታ አካሉ ሚናውን ተወጥቷል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላምን በማጽናት የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ የፀጥታ አካሉ ሚናውን ተወጥቷል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን።

የክልሉን ወቅታዊ የሠላም ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች በተመለከተ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የፀጥታ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት÷ የክልሉን ሠላም በማጽናት የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የፀጥታ ሃይሉ ሁልጊዜም ዝግጁ ነው።

ቀደም ሲል በክልሉ ተከስቶ የነበረው የሠላም እጦት ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የጸጥታ ሃይሉ ከክልሉ ሕዝብ ጋር በመቀናጀት ባከናወናቸው ተግባራት የክልሉ ሠላም መመለሱን ነው ያስረዱት፡፡

በዚህም ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ለተገኘው ሠላምና የልማት እንቅስቃሴ የፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ አሰራር የጎላ ሚና ስላለው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የክልሉ ሠላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ በበኩላቸው÷ የፀጥታ አካላት ሠላምን ለማስፈን የከፈሉት መስዋዕትነት በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

የሠላም ተመላሾችም በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ በመሆን የኢኮኖሚ አቅማቸውን እያሳዳጉ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.