ኦስማን ዴምቤሌ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የ2025 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡
የ2025 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በዚህም ኦስማን ዴምቤሌ የባሎንዶር ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡
ፍራንስ ፉትቦል በሚያዘጋጀው የባሎንዶር ሽልማት ሥነ ሥርዓት የፒኤስጂው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የወርቅ ኳሱን ከሮናልዲኒሆ ጎቹ እጅ ተረክቧል።
ድንቅ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ፈረንሳዊው ተጫዋች ዴምቤሌ ፒኤስጂ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያነሳ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
በሬኔስ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባርሴሎና ወደመሳሰሉት ትልልቅ ቡድኖች ተዛዋውሮ መጫወት የቻለው ዴምቤሌ በፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል።
በተመሳሳይ ስፔናዊው የፒኤስጂ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆኖ ሲመረጥ፥ጣልያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሆኖ ተመርጧል፡፡
በሌላ በኩል የአርሰናሉ አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬሽ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ ሆኖ በመመረጥ ሽልማቱን ከሉዊስ ፊጎ እጅ ተረክቧል፡፡