Fana: At a Speed of Life!

ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ግራሃም ፖተርን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የለንደኑ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ግራሃም ፖተርን ከኃላፊነታቸው አሰናብቷል፡፡
አሰልጣኙ ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ክለቡን ከተረከቡ ወዲህ በቆይታቸው ካደረጉት 25 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት ስድስቱን ብቻ ነው፡፡
ዌስትሃም በፖተር ምትክ በቅርቡ ከኖቲንግሃም ፎረስት የተሰናበቱትን ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን አሰልጣኙ ለማድረግ በንግግር ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዌስትሃም ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ በሦስት ነጥብ 19 ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ ከወዲሁ ከካራባኦ ዋንጫ ውጭ ሆኗል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.