Fana: At a Speed of Life!

ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል ውሉን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል ለተጨማሪ አምስት አመታት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡

ሪያል ማድሪድ የ24 ዓመቱን ተጫዋች ለማስፈረም ጥብቅ ፍላጎት እንዳለው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ሆኖም ተጫዋቹ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በኢምሬትስ ለመቆየት የተስማማ ሲሆን፥ በመጪው ክረምት የሚያበቃውን ውሉን አድሷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ካሉ አስደናቂ የመሃል ተከላካዮች መካከል አንዱ የሆነው ዊሊያም ሳሊባ፥ ሪያል ማድሪድ ያሳየውን ፍላጎት ውድቅ በማድረግ ከአርሰናል ጋር ለመቆየት መስማማቱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.