በኮፕ30 የአፍሪካን አቋም ለማስተጋባት ሩሲያ ድጋፍ ታደርጋለች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ኢቭጌኒ ተርክሂን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ውይይታቸውም የአፍሪካ ህብረት- ሩሲያ ትብብር፣ ለሁለተኛው የሩሲያ አፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ዝግጅት፣ የሳህል ቀጣና ሃገራት እድገት፣ አፍሪካ ህብረት የሚመራው የሶማሊያ ሰለም ጥበቃ እና አቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ሁለቱ ወገኖች በፈረንጆቹ 2025 ሕዳር ወር ላይ በብራዚል በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ30) የአፍሪካን አቋም ለማስተጋባት ትብብር ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
ሊቀመንበሩ ሩሲያ በመህር ላይ ተመስርታ በተባበሩት መንግስታት ጸጥታው ምክር ቤት ጭምር ለአፍሪካ ሀገራት ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደር ተርክሂን በበኩላቸው በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ አህጉር በዓለም መድረክ ትኩረት እንዲያገኝ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ላደረገው ጥረት አድናቆታቸውን ችረዋል።