Fana: At a Speed of Life!

የቦካ ጁኒየርስ አሰልጣኝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየርስ ዋና አሰልጣኝ ሚጉኤል ሩሶ በ69 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የፕሮስቴት ካንሰር ታማሚ ሆነው የቆዩት አሰልጣኙ÷ ባለፉት ዓመታት ከሕመማቸው ጋር እየተጋሉ ሥራቸውን ሲያከናውኑ እንደነበር ክለቡ አስታውቋል፡፡

ሚጉኤል ሩሶ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያመሰገነው ክለቡ÷ በሕልፈታቸው የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

የቦካ እና ዩራጓይ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ በአሰልጣኙ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጾ ፤ ስለሁሉም ነገር እናመሰግናለን ብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.