ዲጂታል ክህሎትን ለማበልጸግና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
24ኛው የኮሜሳ የመሪዎች ጉባኤ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂና አካታች እድገት ማዋል” በሚል መሪ ሀሳብ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል ማቅረቡን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመርና ቀጣናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክህሎቱና መሠረቱ አለን ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ ዲጂታል ክህሎትን ለማበልጸግና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!