ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች እያደረገች ትገኛለች – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትጵያ ለዓለም አቀፍ አጋሮች ምቹ የገበያ ከባቢን በመፍጠር ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች እያደረገች ትገኛለች አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በቤልጂየም እየተካሄደ ባለው 2ኛው የግሎባል ጌት ዌይ ፎረም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል፣ ዲጂታላይዜሽን እና ዘላቂ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለዓለም አቀፍ አጋሮች ምቹ የገበያ ከባቢን በመፍጠር ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች እያደረገች እንደምትገኝም አስገንዝበዋል።
በዓለም አቀፉ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ አንድ ሀገር የሚጫወተው ሚና በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነት እና ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ባለው ግንኙነት መሆኑን አንስተው÷ ኢትዮጵያም በዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ናት ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለግሎባል ጌትዌይ ዝግጁ ናት ያሉት ፕሬዝዳንቱ÷ ለዚህም በታዳሽ ኃይል፣ ምቹ የኢንቨስትመንት ሥነምህዳር በመገንባት እና ስትራቴጂካዊ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየሰራች ያለውን ሥራ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ውጤት ተኮር ግቦች ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመስራቷም ባለፈው ወር ያስመረቀችው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማሳያ ነው ብለዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!