Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተቀረጹ የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና ኢኒሼቲቮች ውጤታማነታቸው እየተረጋገጠ ነው – አቶ ኡስማን ሱሩር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቀረጹ አዳዲስ የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና ኢኒሼቲቮች በአጭር ጊዜ በሁሉም አካባቢ ተተግብረው ውጤታማነታቸውን እየተረጋገጠ ነው አሉ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ግብርና ሴክተር የ2017 አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ” የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው።

ኡስማን ሱሩር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ግብርና ለአትዮጵያ ኢኮኖሚ ግንባታና ሀገራዊ ማንሰራራትን ለማፋጠን ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት የክልሉ ግብርና ቢሮ ግብርናን ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው÷ በዚህም ተስፋ ሰጪ የምርታማነት እድገትና የህዝብ ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መሻሻል በመኖሩ በሁሉም የግብርና ምርቶች የምርታማነት ዕድገት መታየቱን አንስተው÷ በወተት፣ እንቁላል፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና አትክልት ከፍተኛ እመርታ የተመዘገበባቸው እንደሆኑ አመላክተዋል።

የምርታማነት ዕድገቱ የገቢ ምርትን በመተካት፣ በገጠር የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ማንሰራራት የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አንስተዋል።

በክልሉ የተቀረጹ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ግብርናን በማዘመን ሀገራዊ የምግብ ሉዓለዊነትን ለማረጋገጥ እና የኢኮኖሚ ማንሰራራትን በማፋጠን ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

በመሆኑም ግብርናን ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎችን አቀናጅቶና አስተባብሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በ2018 የበጋ ወቅት የምርታማነት ልዩነቶችን ለማጥበብ የተቀናጀ የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማንሰራራት እናፋጥናለን ማለታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኑረዲን ፈይሳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.