Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ባራሕሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

የሰሜናዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ አስሓብ የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል።

በሁለቱ ወረዳዎች መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ለተጎጂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

የባራሕሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን በበኩላቸው÷ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በአደጋው እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ማለፉን ገልጸው÷ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አስረድተዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ መቅረታቸውን ጠቁመዋል።

ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

በአሊ ሹምባሕሪ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.