በሶማሌ ክልል የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል በቅርቡ የተመረቁና የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የዲጂታል ሚዲያ ዳይሬክተር አቶ ቢሻር ሞሐመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የድጋፍ ሰልፉ በዛሬው ዕለት በክልሉ በሚገኙ 95ቱም ወረዳዎች እና ስድስቱ ከተማ አስተዳደሮች ነው የተካሄደው።
የድጋፍ ሰልፉ መንግሥት በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ በመጀመሩና ከዚህ በፊት የነበረባቸውን ጥያቄዎች እየመለሰ በመሆኑ እንደሆነ አንስተዋል።
በዚህም አሁን ላይ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ በመሆኑ ደስተኛ እንደሆኑና ለመንግሥት ያላቸውን አጋርነት ለማረጋገጥ ያለመ ሰልፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!