ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ያገኘችው እውቅና የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ውጤት ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያገኘችው ዓለም አቀፍ እውቅና የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ውጤት ነው አሉ የመርሐ ግብሩ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር)፡፡
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም በሚል ዘርፍ እውቅና ሰጥቷል።
አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በመርሐ ግብሩ አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን ችግር በመረዳት መፍትሄ ለማምጣት ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን ችላለች።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ ብቻ ሳይሆን ለምግብ ዋስትና፣ ለደን ልማትና መሰል ዘርፎች አበርክቶው የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመራበት አግባብ፣ ለዓለም ስነ ምህዳር ያበረከተው ትሩፋትና ህዝቡ ያሳየው የነቃ ተሳትፎ ታይቶ ለሽልማት መብቃቱን ነው አስተባባሪው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከል በራሱ የእውቅናው አንደኛው መስፈርት መሆኑን ጠቅሰው፥ በርካታ ሀገራት ይህንን ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ለመውሰድ ፍላጎታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት፡፡
አሁን በመርሐ ግብሩ የተገኘው እውቅና ለሌሎች የልማት ተግባራት የሚያነሳሳ እና የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!