Fana: At a Speed of Life!

አግልግሎት አሰጣጥን ከብልሹ አሰራር የማጽዳት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

‎አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥት አግልግሎት አሰጣጥን ከብልሹ አሰራር የማጽዳት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።

‌‎ርዕሰ መስተዳድሩ የሚዛን አማን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዲጂታሉ ዓለም ጋር በመራመድ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ነው።

ማዕከሉ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው÷ በሌሎች አምስት የክልሉ ከተሞች ተጨማሪ ማዕከላት ይገነባሉ ብለዋል።

‎ከ350 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ÷ 32 አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚችልና በቀጣይ 50 ለማድረስ እንደሚሰራ ተገልጿል።

‎የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ በበኩላቸው÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

‎በሀገር አቀፍ ደረጃ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች 18 መድረሳቸውን አንስተው÷ በክልሉ ሌሎች ማዕከላት ተከፍተው ዜጎች የመንግስትን አገልግሎት በክብር እንዲያገኙ ኮሚሽኑ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

‎በፍሬው አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.