Fana: At a Speed of Life!

60 በመቶ የካንሰር ሕክምና ወጪ የሚሸፈነው በመንግሥት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ሕክምና ወጪ የሚሸፈነው በመንግሥት ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጤና አገልግሎትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንዳሉት፥ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ሰፊ ስራ የተሰራ ቢሆንም ቀሪ ስራዎች አሉ።

63 ሚሊየን ገደማ ዜጎች በጤና መድህን ስርዓት ታቅፈው አገልግሎት እያገኙ እንደሆነም ተናግረዋል።

የመድሐኒት አቅርቦትን በተመለከተም ከውጭ የሚገባውን ለመቀነስ በሀገር ውስጥ መድሐኒት እየተመረተ እንደሆነ ገልጸው፥ መንግሥት የመድሐኒትን አቅርቦትን ለመደጎም 60 ቢሊየን ብር መመደቡን ገልጸዋል።

የካንሰር ህሕምናን ለማሳደግ ከሚሰራው ስራ በተጨማሪ የሕክምና ወጪን እየሸፈነ መሆኑን ገልጸው፥ 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ሕክምና ወጪ የሚሸፈነው በመንግሥት ነው ብለዋል።

በጳውሎስ ሆስፒታል 1 ሺህ አልጋ ያለው መሰረተ ልማት ተገንብቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፥  ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.