ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባ ምንጭ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የኢትዮ ኤሌክትሪክን ግቦች በፍቃዱ አስረሳኸኝ ፣ ሀሰን ሁሴን እና አቤል ሀብታሙ ሲያስቆጥሩ፥ አርባ ምንጭ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ይገዙ ቦጋለ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ምድረ ገነት ሽረ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል መቻል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል፡፡