Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ውስጥ የተመረተ “ቶሎ” የተሰኘ ሃይል ቆጣቢ የኤሌክትሪክ ምድጃ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር ውስጥ የተመረተ “ቶሎ” የተሰኘ ሃይል ቆጣቢ የኤሌክትሪክ ምድጃ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

ግሪን ሲን ኢነርጂ በተባለ ተቋም የተመረተው ቶሎ የኤሌክትሪክ ምድጃ የሃይል ፍጆታን 50 በመቶ መቀነስ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

የግሪን ሲን ኢነርጂ ሥራ አስኪያጅ ረቂቅ በቀለ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉት ሃይል ቆጣቢ ምድጃዎች በኤሌክትሪክና በሶላር የሚሰሩ ናቸው ፡፡

እነዚህ ምድጃዎች የሃይል ፍጆታን በመቀነስ በተለይም ለገጠሩ የሕብረተሰብ ክፍል ዘመናዊ ምድጃዎችን ተደራሽ በማድረግ የአኗኗር ዘያቸውን ለማቅለል ጉልህ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት ታዳሽ ኃይልን በኃይል ምንጭነት የመጠቅም ተሞክሮን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት፡፡

“ቶሎ” ሃይል ቆጣቢ የኤሌክትሪክ ምድጃ የሚባክንን የኤሌክትሪክ ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ ምደጃው በ10 የተለያዩ አማራጮች እየቀረበ ሲሆን÷የምርቱን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋትም አጋር አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.