ድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ቀን 9:00 ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሲዳማ ቡና እና ምድረ ገነት ሽረን 2 ለ 1 አሸንፏል።
የሲዳማ ቡና ግቦችን ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን እና ብርሃኑ በቀለ ሲያስቆጥሩ፤ የምድረ ገነት ሽረን ግብ አቤል ማሙሽ ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ሜዳ ምሽት 12:00 ላይ በተካሄደው የድሬዳዋ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ 2 ለ 1 ተጠናቅቋል።
የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ታደሰ እና አብዱሰላም የሱፍ ከመረብ ሲያገናኙ፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ዳዊት ገብሩ አስቆጥሯል።
ቀን 9:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የኢትዮጵያ መድን እና አርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።