ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ከአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
ምክክሩም ባንኩ በመላው አፍሪካ አካታች እድገት እንዲኖር የሚያደርገውን ወሳኝ ሚና ያጠናከረ እንደነበር አመልክተዋል፡፡
ውይይቱ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ከሚገኘው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡