በሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
አደጋው ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ በሕገ ወጥ ደላላዎች ተታልለው ወደ ውጭ ሀገራት ለማቅናት የተሰባሰቡ ሰዎችን የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ ሰመራ ከተማ አደባባይ ላይ በመገልበጡ ነው የደረሰው።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊ ቢኢዶ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በተከሰተው አደጋ እስካሁን የ22 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸው፤ ከሟቾች በተጨማሪ 30 ሰዎች ላይ ከባድ እና 35 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ተጎጂዎችን ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን አስገንዝበዋል።
ወጣቶች በሕገ ወጥ ደላላዎች በመታለል ለመሰል አደጋ ራሳቸውን ማጋለጥ እንደሌለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!