Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ነው ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ጨዋታቸውን ያጠናቀቁት።

ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያለ ምንም ግብ ወደ እረፍት አምርተዋል።

የዕለቱ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ መድን ይገናኛል።

ቀምድ ሲል በተካሄደው የሊጉ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.