Fana: At a Speed of Life!

የባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል ‘ሾልኣ-ካሻ’ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል ‘ሾልኣ-ካሻ’ በላስካ ከተማ በአደባባይ እየተከበረ ነው።

“‎ባህላዊ እሴቶቻችን ለትውልድ ግንባታና ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው ዓመታዊ የምስጋና በዓል ‘ሾልኣ-ካሻ’ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የባስኬቶ ዞን ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

‘ሾልኣ-ካሻ’ የልዩነት አጥሮችን በማፍረስና ግላዊ እይታዎችን በማምከን ለጋራ ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጥበት የምስጋና በዓል መሆኑ ተገልጿል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሳለኝ እንዳሉት፤ ‎የአንድነት፣ የህብረትና የምስጋና በዓል የሆነው ‘ሾልኣ-ካሻ’ በዓል ሀገራዊ አንድነትንና አብሮነትን ለማጽናት የጎላ ሚና ይጫወታል።

‎የባስኬት ብሔረሰብን ባህልና ወግ ለመላው ዓለም ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ‘ሾልኣ-ካሻ’ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ ለማስተዋወቅ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉ ፓናል ውይይትን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱን ለፋና ዲጂታል የገለጹት ደግሞ የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ኃይለኢየሱስ አባይነህ ናቸው።

‎የባስኬት ብሔረሰብ በየዓመቱ የምርት መድረስና መሰብሰብን ተከትሎ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ‘ሾልኣ-ካሻ’ ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላለፍ ምሁራን እና የአከባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.