Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር የኤሌክትሪክ የከተማ አውቶብሶች በይፋ ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 10 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ የከተማ አውቶብሶች በባህር ዳር ከተማ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡

የነዳጅ ወጪና የውጭ ምንዛሪን ለማስቀረት እንዲሁም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ መንግሥት በያዘው እቅድ መሠረት በተለያዩ ከተሞች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት አገልግሎት ላይ እየዋሉ ነው።

በዚህም መሰረት የባህር ዳር ከተማ ከተማ አሥተዳደር በቢኬጅ የተገጣጠሙና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ 10 ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶብሶችን ተረክቧል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የተገጣጠሙት እነዚህ የከተማ አውቶብሶች በባህር ዳር ስራ መጀመራቸው በከተማው በአሁኑ ሠዓት የሚታየውን ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት እንደሚያቃል ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መሆናቸው ከከተማዋ ዘመናዊ እሳቤ ጋር የሚጣጣሙና ከብክለት እንደሚታደጉ ይታመናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.