Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ነገሌ አርሲን 2 ለ 0 አሸንፏል።

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን ግቦች ሽመልስ በቀለ እና ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቀደም ብለው በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ምድረ ገነት ሽረ አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0፣ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 2 ሲያሸንፉ÷ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.