Fana: At a Speed of Life!

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሦስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።

አቤል ጌትነት፣ አሮን ሀይሉ፣ ግዛቸው አማረ እና ታፈረ አሰፋ የፍጻሜ ውድድሩ ተፋላሚዎች ሲሆኑ÷ በሦስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከኮከብ ባንድ ጋር የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለእነዚህ ተወዳዳሪዎች የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።

በዚህ መሰረትም አንደኛ ደረጃን ለሚይዝ 400 ሺህ ብር ፣ 2ኛ ደረጃን ለሚያገኝ 300 ሺህ ብር ፣ 3ኛ ደረጃ ለሚወጣ 200 ሺህ ብር እና 4ኛ ደረጃን ይዞ ለሚያጠናቅቅ ደግሞ 100 ሺህ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

አራቱ የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ለ6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ላይ አንድ ተወዳጅ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይገኛል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አድማጭ ተመልካቾች የቅዳሜውን የፍጻሜ ውድድር በሁለቱም የፋና ቴሌቪዥን ቻናሎች እንዲሁም በፋና ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲከታተሉ ይጋብዛል፡፡

ቅዳሜ ከ6 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩን በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ ለተወዳዳሪዎች ድጋፍ ማድረግ ይቻላል፡፡

በለምለም ዮሃንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.