አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዌንካይ ዣንግ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዌንካይ ዣንግ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ እና በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ውህደትን ለማሳለጥ እየሰራ የሚገኘውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አብራርተዋል፡፡
ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ በበኩላቸው÷የኢትዮጵያ መንግሥት የብድር ማሻሻያ ግንባታን ጨምሮ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር ላሳየው ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ልማት አጀንዳዎችን በዘላቂነት በቴክኒክ እና በፋይናንስ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ የአጋርነት ሒደት መገምገማቸውንም ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የበጀት ድጋፍ ሥራ እና የፕሮጀክቶች ፋይናንስ ከሀገራዊ የልማት አላማዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንደሚከናወን አጽንኦት ሰጥተዋል።