የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሦስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል።
አቤል ጌትነት፣ አሮን ሀይሉ፣ ግዛቸው አማረ እና ታፈረ አሰፋ የፍጻሜ ውድድሩ ተፋላሚዎች ሲሆኑ÷ በሦስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከኮከብ ባንድ ጋር የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተወዳዳሪዎቹ የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
በዚህም መሰረት ውድድሩን በአንደኛ ደረጃ የሚያጠናቅቅ 400 ሺህ ብር፣ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ደግሞ የ300 ሺህ፣ የ200 ሺህ እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ፡፡
አራቱም የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ለ6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ላይ አንድ ተወዳጅ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይገኛል።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አድማጭ ተመልካቾች የቅዳሜውን የፍጻሜ ውድድር በሁለቱም የፋና ቴሌቪዥን ቻናሎች እንዲሁም በፋና ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲከታተሉ ይጋብዛል፡፡
ቅዳሜ ከ6 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩን በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።