የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎችን አጓጉዟል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ስድስት ወራት 10 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎችን አጓጉዟል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፥ በአገልግሎት ዘርፍ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።
በለውጡ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት በአማካኝ 8 ሚሊየን ሰዎች ያጓጉዝ ነበር እንደነበር አስታውሰው፤ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ 10 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎችን አጓጉዟል ብለዋል።
በዚህ ዓመት ቢያንስ 22 ሚሊየን ለመድረስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ማሳካት ከተቻለ በለውጡ ወቅት ከነበረው አንጻር በሁለት እጥፍ በላይ እንደሚያድግ ተናግረዋል።
አየር መንገዳችን በቁጥር፣ በመዳረሻ፣ በትርፍ፣ በሚያጓጉዘው ሰው ጨምሯል ሲሉም አብራርተዋል።
በሶስና አለማየሁ