Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ እንግዶችን ልቧን ከፍታ እጆቿን ዘርግታ ትቀበላለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ተሳታፊ እንግዶችን ልቧን ከፍታ እጆቿን ዘርግታ ትቀበላለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ውድ ኢትዮጵያዊያን ፣ በዚህ ሳምንት ውዷ ሀገራችን በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የሚመጡ እህት ወንድም አፍሪካዊያንን ለማስተናገድ ልቧን ከፍታ-እጆቿን ዘርግታ ትቀበላለች ብለዋል።

እነዚህ ወዳጆቻችን የሰንደቃችንን ቀለማት የሚጋሩ፣ ኢትዮጵያን እንደነፃነት ቀንዲል የሚመለከቱ ብሎም ሀገራችን የአኅጉሩ የፖለቲካ ርዕይ የማዕዘን ድንጋይ አድርገው የሚያከብሩ ናቸው በማለት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደር በሌለው እንግዳ ተቀባይነቷ ለምን ልትከበር እንደበቃች በአቀባበላችን እናሳያቸው፤ እንደቤታቸው እንዲሰማቸው እናድርግ ነው ያሉት።

በክብር እንቀበላቸው፤ በፍቅር እናቆያቸው፤ ተደምረን ሰንደቃችን የሚወክለውን የአፍሪካ አንድነትን መንፈስ እና የሚያያይዘንን የወል ህልም እናክብር ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.