የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እንዲሁም የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽሕና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ÷ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነገና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።