ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን ክርስቲያን አውር ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
በተለይም ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፉን ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት አምባሳደሩ እንደሚደግፉ መናገራቸውን ከውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡