በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የአካል ጉዳተኞች፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተሳትፎ
እነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን የዴሞክራሲ ተሳትፎና ውክልና እንዲኖራቸው በተለየ ሁኔታ ትኩረት ያሻቸዋል፡፡
ስለሆነም የእነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሁኔታ በተገቢው ተጠንቶ የመራጮች ትምህርት እንዲያገኙ፣ በመራጭነት/ተመራጭነት እንዲመዘገቡ እና እንዲመርጡ የሚያስችል እቅድ ወጥቶ ይተገበራል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያፀደቀችው ዓለም ዓቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን፤ የአካል ጉዳተኞችም በፖለቲካው መስክ በነፃነት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት በመምረጥና በመመረጥ ከሌሎች ጋር ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚኖርባት ይደነግጋል፡፡
በዚህ ረገድ መንግስት የአካል ጉዳተኞች:-
👉የምርጫ አሰራሮች፤
👉ቁሶችና ስፍራዎች ለአካል ጉዳተኞች ተስማሚ እንዲሆኑ፤
👉ድምጻቸውን በነፃነትና በምስጢር የሚሰጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
👉እርዳታ የሚሹ በሚመርጡት ሰው የመታገዝ መብት እንዲኖራቸው ፤
👉ተመርጠው በማናቸውም ደረጃ የማገልገል ዕድል እንዲኖራቸው ፤
👉አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ እና
⚙️በአጠቃላይ የአካል ጉዳተኞች ያለ አድልዎ ከሌሎች ጋር በእኩልነት በፖለቲካና እና በሕዝብ አስተዳደር ጉዳዮች እንዲሳተፉ ማድረግና ማበረታታት ያለበት መሆኑ በኮንቬንሽኑ አንቀፅ 29 ሥር ተደንግጓል፡፡
የምርጫ አዋጅ ቁ. 1162/2011 በምርጫ ወቅት የኮንቬንሽኑ አንኳር ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
አዋጁ የአካል ጉዳተኞች የጉዳት ዓይነት በመራጮች መዝገብ ላይ እንዲገለፅ ከማድረግ አንስቶ ለዕጩነት ለመቅረብ የሚያስፈልገው የድጋፍ ፊርማ ብዛት ከሌሎች ዕጩዎች ያነሰ እንዲሆን፡፡
እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚያደርጉት ተሳትፎ ከፍ እንዲል እነርሱን በአባልነት በዕጩነት እና በአመራርነት ለሚያሳትፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግበት የማበረታቻ ሥርዓት ዘርግቷል፡፡
አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦችንና ሕዝቦችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
ይህም የእነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች በፌዴራል የሕግ አውጪው አካል ውስጥ ውክልና እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡